በአገልግሎት ላይ

ለጅጅጋ-ደገሐቡር አካባቢዎች የገጠር ኤሌክትሪክ ስርጭት ኘሮጀክት ማስፈፅሚያ ከኦፔክ ፈንድ ለአለም አቀፍ ልማት የተገኘው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለጅጅጋ-ደገሐቡር አካባቢዎች ገጠር ኤሌክትሪክ ሥርጭት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 20 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር (ሃያ ሚሊዮን የአሜሪካ የአሜሪካ ዶላር) የሚያስገኘው ብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኦፔክ ፈንድ ለዓለም አቀፍ ልማት መካከል እ.ኤ.አ ጁላይ 7 ቀን 2010 በቪየና የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ጥር 3 ቀን 2003 ዓ.ም ባካሔደው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 702/2003
ቀን: የካቲት 4፥ 2003 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች