ለአርባረከቲ-ገለምሶ ሚቸታ የመንገድ ሥራ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (ሃያ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በኦፔክ ፈንድ ለዓለም አቀፍ ልማት መካከል እ.አ.አ ሜይ 30 ቀን 2013 በማራኪሽ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 20 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡