በአገልግሎት ላይ

ለሀሙሲት-እስቴ የመንገድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ብድር ከነዳጅ አምራችና ላኪ አገራት ፈንድ ለዓለም አቀፍ ልማት ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለሀሙሲት-እስቴ የመንገድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 20 ሚሊዮን (ሃያ ሚሊዮን) የአሜሪካን ዶላር የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በነዳጅ አምራችና ላኪ አገራት ፈንድ ለዓለም አቀፍ ልማት መካከል እ.አ.አ ኖቬምበር 9 ቀን 2016 በቪየና የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 997/2009
ቀን: መጋቢት 1፥ 2009 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች