በአገልግሎት ላይ

ከኦፔክ ፈንድ ለዓለም አቀፍ ልማት ጋር የተደረገው የዕዳ ቅነሳ ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለዕዳ ክፍያ የሚውል 6,500,000 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) በብድር የሚያስገኘው የዕዳ ቅነሳ ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኦፔክ ፈንድ ለዓለም ዐቀፍ ልማት መካከል እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 21 ቀን 2005 በቪየና የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 522/1999
ቀን: ግንቦት 7፥ 1999 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች