በአገልግሎት ላይ

ለቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ክህሎት ማሻሻያ እና ሥራ ፈጠራ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል ብድር ከጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ክህሎት ማሻሻያ እና ሥራ ፈጠራ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 8 ሚሊዮን ዩሮ (ስምንት ሚሊዮን ዩሮ) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግስት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1199/2012
ቀን: ግንቦት 14፥ 2012 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች