የተሻረ

ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ

መንግሥት ለሕዝብ አገልግሎት ለሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች መሬትን መጠቀሙ አስፈላጊ ስለሆነ፣

የአገሪቱ ከተሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉና የነዋሪዎችም ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ በከተሞቹ ፕላን መሠረት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለመሠረተ ልማት፣ ለኢንቨስትመንትና ለሌሎች አገለግሎቶች የሚውል የከተማ መሬትን መልሶ ማልማት አስፈላጊ በመሆኑ፣ እንዲሁም በገጠር ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች መሬት አዘጋጅቶ ማቅረብ በማስፈለጉ፣

የመሬት ይዞታ እንዲለቀቅ ሲደረግ ለባለይዞታው የሚከፈለውን ካሣ ለመተመን እንዲቻል ግምት ውስጥ መግባት የሚገባቸውን መሠረታዊ መርሆዎች ለይቶ መወሰን በማስፈለጉ፣

ካሣውን የመተመን ሥልጣንና የመክፈል ኃላፊነት ያለባቸውን አካላት በግልጽ ለይቶ መወሰን በማስፈለጉ፣ የፌዴራል መንግሥቱ የመሬት አጠቃቀም ሕግ የማውጣት ሥልጣን እንዳለው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 51 (5) በመደንገጉና ለሕዝብ ጥቅም የሚለቀቅ ንብረትን በሚመለከት በቅድሚያ ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፈል በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 (8) የተቀመጠውን መሠረተ ሃሳብ በመመርኮዝ በዝርዝር መደንገግ በማስፈለጉ፣

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 455/1997
ቀን: ሐምሌ 8፥ 1997 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1336/2016

ሐምሌ 4፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1161/2011

መስከረም 19፥ 2011 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 516/1999

የካቲት 12፥ 1999 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 378/1996

ታህሳሰ 13፥ 1996 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ