በአገልግሎት ላይ

ለስኳር ኢንድስትሪ ልማት ኘሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል ተጨማሪ ብድር ከሕንድ የኤክስፐርት ኢምፖርት ባንክ ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለስኳር ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ 47 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (አርባ ሰባት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በሕንድ የኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል እ.ኤ.አ ኤፕሪል 12 ቀን 2012 በኒውዴልሂ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 755/2004
ቀን: ሐምሌ 20፥ 2004 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations
Sector: Development

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች