ለስኳር ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 122 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በሕንድ የኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ መካከል እ.ኤ.አ ኦክቶበር 4 ቀን 2007 በኒው ዴልሂ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ህዳር 26 ቀን 2000 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•