ለአዳማ (ናዝሬት) የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 99 ሚሊዮን 450 ሺ የአሜሪካን ዶላር (ዘጠና ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሣ ሺ የአሜሪካን ዶላር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በቻይና የኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ መካከል እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 23 ቀን 2010 የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ታህሣሥ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•