የፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ላይ የተደረገውን ለውጥ ተከትሎ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011አንቀጽ 32(11) መሰረት የተቋቋመ በመሆኑ፣
የፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የኢንስቲትዩቱን ስልጣንና ተግባር በአንድ ላይ በማሰባሰብ የኢንስቲትዩቱን አደረጃጀት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤
ለኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲቲዩት፣ እና ለፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ሁሉ ለፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተሰጥተዋል በሚል በመቀመጡ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በፌደራል መንግስት አስፈጻሚአካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 ዓ.ም አንቀጽ ፴፬ መሰረት የሚከተለውን ደንብ አውጥቷል፡፡
•
•
•
•
•
•
•