በአገልግሎት ላይ

ስደተኛ የዱር እንስሳት ዝርያዎችን ለመጠበቅ የተፈረመው ዓለም ዓቀፍ ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

ዓለም ዓቀፍ ስደተኛ የዱር እንስሳት ዝርያዎች ለመጠበቅ እ.ኤ.አ. ጁን 23 ቀን 1979 በጀርመን አገር በቦን ከተማ ተፈርሞ ከኖቬምበር 1 ቀን 1983 ጀምሮ በሥራ ላይ የዋለ በመሆኑ፤

ስምምነቱም ስደተኛ የሆኑ የዱር እንስሳት ዝርያዎችን በአባል አገራት ትብብር ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚኖረው በመሆኑ፤

ኢትዮጵያ ስምምነቱን መቀበሏ ለዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ጠቃሚ መሆኑ ስለታመነበት፤

በዚህም የስምምነት አንቀፅ 17 እ.ኤ.አ. ከጁን 22 ቀን 1980 በኋላ አባል ለመሆን ፈቃደኛ የሆኑ አገራት ስምምነቱን በማፅደቅ አባል ለመሆን ስለሚችሉ፤

ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 27 ቀን 2001 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀፅ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 634/2001
ቀን: ሰኔ 23፥ 2001 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 373/1996

ጥቅምት 17፥ 1996 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 114/1990

ግንቦት 25፥ 1990 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 90/1990

ጥቅምት 13፥ 1990 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 55/1989

ታኅሣሥ 08፥ 1989 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ