ለአሶሳ-ኩርሙክ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 6 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት መካከል እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 16 ቀን 2005 ካርቱም የተፈረመ በመሆኑ፤
መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም ዐቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት መፅደቅ ስላለባቸው፣
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 15 ቀን 1998 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•