በአገልግሎት ላይ

ለደብረማርቆስ-ሞጣ የመንገድ ሥራ ማሻሻያና ማሳደጊያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ብድር ከሳዑዲ የልማት ፈንድ ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለደብረማርቆስ – ሞጣ የመንገድ ሥራ ማሻሻያና ማሳደጊያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 281 ሚሊዮን 250 ሺህ የሳዑዲ ሪያል (ሁለት መቶ ሰማኒያ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ የሳዑዲ ሪያል) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በሳዑዲ የልማት ፈንድ መካከል ታህሳስ 9 ቀን 2011 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1195/2012
ቀን: ግንቦት 14፥ 2012 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች