ለጐዴ-ቀብሪደሃር አካባቢዎች የገጠር ኤሌክትሪክ ሥርጭት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 56 ሚሊዮን 250 ሺህ የሳውዲ ሪያል (ሃምሳ ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ የሳውዲ ሪያል) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በሳውዲ የልማት ፈንድ መካከል እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2013 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡