በአገልግሎት ላይ

ለነጆ-መንዲ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከኦፔክ ዓለም አቀፍ ልማት ፈንድ ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

ለነጆ-መንዲ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 9 ሚሊዮን 500 ሺህ (ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) የአሜሪካን ዶላር የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኦፔክ ዓለም አቀፍ ልማት ፈንድ መካከል እ.ኤ.አ ዲሴምበር 21 ቀን 1999 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት መጽዴቅ ስላለባቸው፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 29 ቀን 1992 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 204/1992
ቀን: የካቲት 28፥ 1992 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች