የመመሪያ መለያ: 129/2014
ቀን: ጥር 18፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የመጀመሪያ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራንና ምክትል ርዕሰ መምህራን የድልድል አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 129/2014

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የታየውን ለውጥ ለማስቀጠልና ዘላቂ ለማድረግ ለተማሪዎች የሚሰጠውን የመማር ማስተማር አገልግሎት ግልጽ፣ፈጣንና ውጤታማ እንዲሆንና ተጠቃሚነትን ለማስፈን በርካታ የለውጥ ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፤ ከነዚህ ለውጦች መካከል ዋነኛው የከተማ አስተዳደሩን የመንግሥት ትምህርት ቤቶች አሠራር እንደገና በማዋቀር ተግባርና ኃላፊነታቸውን የሚመጥን መዋቅራዊ አደረጃጀትና የመሠረታዊ የስራ ሂደት ክለሳ ጥናት አካሂዷል፡

በዚህም መሠረት ለተዘጋጁ የሥራ መደቦች ከመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ጋር የሚጣጣም የአፈፃፀም መመሪያና ቅደም ተከተልን መሠረት ያደረገ ጥናት ለየሥራ መደቦቹ በተሰጠው ደረጃ ዋና ርዕሰ መምህራንና ምክትል ርዕሰ መምህራንን መደቦች ላይ ብቃት ያላቸውን የትምህርት ቤት አመራሮች በውድድር ለመመደብ እንዲያስችል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ በመንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር56/2010 አንቀጽ 97 ንዑስ አንቀጽ(2) እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (3) ተራ ፊደል (ሠ)በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Public Service and Human Resource Development Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration