
ጌታነህ ሀብታሙ በፍትሕ ሚኒስቴር የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ከሀምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በማገልገል ላይ ይገናል። በዚህ ኃላፊነት ማገልገል ከመጀመሩ አስቀድሞ በሕግ ጥናት ማርቀቅ እና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀነራል የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ፖሊሲ እና የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ማስተባበሪያ አስተባባሪ፣ የሕግ ጥናትና ምርምር ማስተባበሪያ አስተባባሪ እንዲሁም ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ በመሆን ከግንቦት 2009 ዓ.ም ጀምሮ በፍትሕ ሚኒስቴር አገልግሏል። ጌታነህ ከፍትሕ ሚኒስቴር በተጨማሪ በፌዴራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በከፍተኛ የሕግ ተመራማሪነት፣ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ዳኛ በመሆን ከሁለት ዓመት (ከህዳር01/2002-ሰኔ 30/2003) የዐቃቤ ሕግነት እና የዳኝነት ሥልጣና በኋላ ከሀምሌ 01/2003 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሏል። ከ15 ዓመት በላይ በክልል እና በፌዴራል የፍትሕ ተቋማት ባካበቱት ልምድ በኢትዮጵያ የሕግ የበላነት እንዲረጋገጥ እና ፍትሕ እንዲሰፍን በቁርጠኝነት ለማገልገል ዝግጁ ናቸው።