የጥብቅና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የጥብቅና ፍቃድ አስተዳደር እና ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከሌሎች በሕግ ከተሰጡት ሥራዎች በተጨማሪ በዋናነት በፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 6/11/ መሠረት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ደረጃ የጥብቅና አገልግሎት ለሚሰጡ ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች በሕግ መሠረት ፈቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ማገድ፣ መሰረዝ፣ ጠበቆችንና የጥብቅና አገልግሎትን ማስተዳደር፣ የነጻ የሕግ አገልግሎት እንዲሰጥ መመደብ፣ የሥነ-ምግባር ግድፈት የታየባቸው ጠበቆች ላይ ክስ ማቅረብ እና መቆጣጠር ዋና ዋናዎቹ ኃላፊነቶቹ ናቸው፡፡

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

ነስሪያ ሱልጣን

ዳይሬክተር