ነስሪያ ሱልጣን ከህዳር 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጥብቅና አስተዳደር እና ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬትን በመምራት ላይ ትገኛለች። አሁን ካለችበት የአመራርነት ተልዕኮ አስቀድሞ የዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አማካሪ በመሆን ስታገለግል የቆየች ስትሆን በዋናነት ግን በክርክር ዘርፉ ላይ ረዘም ላሉ አመታት በኢኮኖሚ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት፣ በሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት እና በልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ተመድባ ሰርታለች፡፡ በዚህም በምርመራ እና በፍርድ ቤት ክርክር የተደራጀ የስራ ልምድ አካብታለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በህግ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዐቃቤያነ ህግ በወንጀል ጉዳዮች የሰጧቸውን ውሳኔዎች በመመርመር ህጋዊነታቸውን የማረጋገጥ እና ውሳኔ ሃሳብ የማቅረብ ስራ ላይም ተመድባ ሃላፊነቷን በተገቢው ለመወጣት ችላለች፡፡ ከ10 አመት በላይ ያካበተችውን የስራ ልምድ በመጠቀም በፍትሕ ዘርፉ ላይ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ ናት።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ የህግ ዲግሪ