ትኩረቱን በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ላይ ያደረገ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል

Training Focused on Human Rights Protection Being Provided

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከጂ.አይ.ዜድ ጋር በመተባበር በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ሪፖርት አቀራረብ እና ሰብዓዊ ስምምነቶች አፈጻጸም ክትትልን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ለፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤያነ ሕግ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ሥልጠናውን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት በሰብዓዊ መብት፣ በሕግ የበላይነት፣ አስተዳደር እና የሽግግር ፍትሕ ዙሪያ የረጅም ጊዜ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን፣ ፍትሕ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብትን ከማስከበር አንጻር በተለይም የሰብዓዊ መብት መከታተያ አካላት የሚሰጧቸውን ምክረ ሃሳቦች ከመከታተል እና ሀገራዊ ሪፖርትን ከማቅረብ አንጻር ውጤታማ ስራ ለመሥራት አጋዥ የሆኑ እውቀቶችና የተኖሩ የህይወት ተሞክሮዎች ቀርበው የጋራ ግንዛቤ ይወሰድባቸዋል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ለአራት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ሥልጠና ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በፍትሕ ሚኒስቴር ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን በመልዕክታቸው ሥልጠናው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 2024 ላይ በሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብት ግምገማ መድረኩ ላይ ከ104 ሀገራት ከተሰጧትን 316 ምክረ ሃሳቦች መካከል የተቀበለቻቸውን 252 ምክረ ሃሳቦች ለመተግበር በዝግጅት ላይ ባለችበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ እውቀቶችን እና ልምዶችን ቀስሞ ለመተግበር ያግዛል ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ተቋሙ 3ኛውን ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ከመከለስ እና የመጀመሪያውን የንግድ እና ሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ከማዘጋጀት አንጻር እስካሁን ድረስ የተከናወኑ ተግበራትን እንዲሁም በማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎችን መብት አያያዝን ከመከታተል አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን ገልጸው ሰልጣኞች በሥልጠናው የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የሚያገኙትን እውቀት እና ልምድ ወደ ተግባር በመለወጥ ሙያዊ ግዴታቸውን እንደሚወጡ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

በሥልጠናው ከፍትሕ ሚኒስቴር የተለያዩ ሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ዐቃቤያነ ሕግ የተሳተፉበት ሲሆን ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡

Tagged Under: attorney Attorney General Capacity Building civil liberties fundamental rights general GIZ human Human Rights human rights implementation human rights monitoring human rights reporting human rights training Implementation law legal Legal Compliance Legal Training monitoring National national human rights action plan Prisoner Rights reporting Rights rule Rule of Law Training transitional justice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች