የወንጀል መከላከል ሀገር አቀፍ ስትራቴጂን ለማስፈጸም የሚያስፈልገውን አደረጃጀት፣ የአሰራር ሥርዓትና የግንኙነት አግባብ የሚቀርጸዉ የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራውን ጀመረ

Technical Committee Commences Work on Drafting Structure, Procedures, and Communication Framework for Implementing National Crime Prevention Strategy

በ2012 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ በሥራ ላይ የሚገኘው ሀገር አቀፍ የወንጀል መከላከል ስትራቴጂን በተመለከተ ስትራቴጅዉን ለማስፈጸም ቁልፍ ሚና ያላቸው ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ግንቦት 8 እና 9 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደዉ አገር አቀፍ የዉይይት መድረክ የተለያዩ አቅጣጫዎች ተቀምጠው የነበረ ሲሆን ከተቀመጡት አቅጣጫዎች አንዱ ስትራቴጂውን ወደ መሬት ለማውረድ የሚያስፈልገው አደረጃጀትና የአሠራር ስርዓት ምን መምሰል አለበት የሚለው ተለይቶ በየደረጃው አደረጃጀቶችና የአሠራር ስርዓቶች ተፈጥረው ወደ ስራ እንዲገባ የሚለው ይገኝበታል፡፡

ይህንኑ መሠረት በማደረግም ከፖሊስ፣ ከፌደራል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ፣ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አገልግሎት፣ ከአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ከፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የተውጣጣ ከፍተኛ ባለሙዎች የተካተቱበት የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስትራቴጅዉን በአግባቡ ለማስፈጸም የሚስፈልገዉን አደረጃጀት፣ የአሠራር ስርዓትና የግንኙነት አግባቡን የሚገዛ ሰነድ የማዘጋጀት ሥራውን በይፋ ጀምሯል፡፡

በሥራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስር ዴኤታ አቶ አለምአንተ አግደው ተገኝተዉ ከቴክኒክ ኮሚቴው የሚጠበቀው በዋናነት ስትራቴጅውን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አደረጃጀቶችን፣ የአሠራር ሥርዓቶችንና በስትራቴጅዉ የታቀፉ ተቋማትን የግንኙነት አግባብ የሚመለከት ምክረ ሀሳብ ማቅረብ እንደሆነ ገልጸው የሚቀርበዉ ሰነድ/ምክረ ሃሳብ የየተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች ያሉበት አብይ ኮሚቴ ተገምግሞ የሚፀድቅ መሆኑን በመግለጽ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ማሳሰቢያ ሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: artificial intelligence institute bishoftou committee communication Coordination Crime federal ethics and anti-corruption commission Federal police financial security service framework Government Officials guidelines Implementation implementation framework interagency interagency coordination justice and law institute National national crime prevention strategy national intelligence and security service policy recommendations prevention procedural procedural guidelines protocols Strategy technical technical committee
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች