የብሔራዊና ክልላዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረቶች የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ለሁለት ቀናት ሲያካሂዱት የነበረዉ የጋራ የግምገማ መድረክ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት እፀገነት መንግስቴ እና በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ በሰጡት የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ተጠናቋል፡፡
በዚሁ ወቅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በትክክል የችግሩን አሳሳቢነት ያገናዘበና ችግሩን ሊቀርፍ የሚያስችል መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ የተነሳ ሲሆን ሁሉም ክልሎች በሚካሄዱ የጋራ ምክክሮች ላይ በመገኘት መሳተፍና የጋራ መፍትሄ አስቀምጦ በቅንጅትና በትብብር መሥራት እንደሚገባቸዉ በተሰጠዉ አቅጣጫ ተመላክቷል፡፡
ብሔራዊ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላየ ግልፀ ሊፈታና ዉጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ እቅዱን ማቀድና የሚደረጉ ድጋፎችን በሚመለከት የአጋር አካላትን ድጋፍ የሚጠናከርበትን ሁኔታ ማመቻቸትና አጋር አካላትን በጥበብ መያዝ እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡
የወንጀል መከላከል ስትራቴጂን በተመለከተም በየ ክልሎቹ እየታዩ ያሉ ጉዳየች እንዴት እየታዩ እንደሆነ የሚያመላክት የጉዳዮች አመራር አገር አቀፍ ዳሰሳ እንደሚደረግና በብሔራዊ ክልላዊ የፍልሰት የትብብር ጥምረቶች ዉስጥ የሚገኙ አምስቱ የስራ ቡድኖች የተነሱ ሀሳቦችን በመዉሰድ በፌዴራልና በክልሎች ተቀራራቢ የሆነ ዕቅድ እንዲኖር በማድረግ በ2017 ዓ.ም የክልል ምክር ቤት ፀ/ቤቶች የሚቋቋምበትን የአደረጃጀትና አሠራር ስራዎች ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
የብሔራዊ የትብብር ጥምረቱ እንደ መንግሥትም ትኩረት የተሰጠዉና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመራቱን እንደ መልካም እድል በመዉሰድ ከፖሊሲ ጋር የሚነሱ ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት ፖሊሲዉ በቶሎ ፀድቆ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑም ተመላክቷል፡፡