የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ 2016 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጻም ግምገማ ተካሔደ

Nine-Month Performance Review of the Attorney General Sector for the 2016 Budget Year Held

በኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጻም ግምገማ መድረክ ሚያዝያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ መድረኩን ሲከፍቱ የዛሬው መድረክ ዓላማ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሚገኙ የስራ ክፍሎች የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈፃፀም መገምገም መሆኑን አውስተው በውይቱም ሁሉም የስራ ክፍሎች በተገኙበት የእያንዳንዱ ስራ ክፍል የስራ አፈፃፀም ምን ይመስላል የሚለውን የምናይበት አንዱ የስራ ክፍል ከሌላው የስራ ክፍል እንዲሁም ፅህፈት ቤቶችም አንዱ ከሌላ የሚማማርበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመድረኩም በዘርፉ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የስራ ክፍሎች ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸውም በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ቀርቧል፡፡

የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታው በየስራ ክፍሎቹ የቀረቡ ሪፖርቶች ስራዎች በምን ያህል ደረጃ እየተሰሩ መሆናቸውን፣ ስራዎችን መሠረት በማድረግ ከተገልጋዩ ማኅበረሰብ እየቀረቡ ያሉ አቤቱታዎች እየቀነሱ መሆናቸውን፣ እንደዘርፍ እየታዩ ያሉ ለውጦች ሊበረታቱ የሚገባቸው በመሆናቸው በቀጣይ ተጠናክረው መሔድ እንዳለባቸው ገልጸው ፣ ዐቃብያነ ሕግ የአሠራር መመሪያና ማኑዋሎችን ተከትለው ስራቸውን በነጻነት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በዘጠኝ ወሩ አፈፃፀም ያጋጠሙ ችግሮችን እንደየስራ ክፍል፣ እንደዘርፍና እንደተቋም መፈታት እንደሚገባ በማንሳት ተቋሙ ምቹ የስራ ሁኔታንና አካባቢን ለመፍጠር ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አክለም ከአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከፍርድ ቤቶች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለው መልካም የስራ ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታው በቀሪ የበጀት ዓመቱ ጊዜያት ቀሪ ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ በማከናወን የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ማሳካት እንደሚገባ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Tagged Under: 2016 2016 budget year Addis Ababa Police administrative reform attorney Attorney General Budget budget performance review case management Courts evaluation Federal police general Justice Justice Ministry Legal Procedures manuals ministry nine-month operational guidelines performance Performance Evaluation public complaints report review Stakeholder Collaboration work plan implementation year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች