ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአስተዳደር ሰራተኞች በፌደራል የሲቪል ሰርቪስ አዋጅ ቁጥር 1064/2010 እና መመሪያዎች ላይ ስልጠና እየሰጠ ነው

Ministry Provides Training to Administrative Staff on Federal Civil Service Proclamation No. 1064/2010 and Related Directives

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለተቋሙ አስተዳደር ሰራተኞች የሲቪል ሰርቪስ አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ዓ.ም ፣ደንብ ቁጥር 77/1994 እና የተለያዩ መመሪያዎች ላይ ሥልጠና ከሚያዚያ 7-8 ቀን 2016 ዓ.ም በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ እንደገለጹት ሥልጠናው ሰራተኞች የተለያዩ መመሪያዎችን፣ ደንቦችን እንዲሁም የፌደራል መንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ዝርዝር ድንጋጌዎችን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባሻገር መብት እና ግዴታቸውን ጠንቅቀው በማወቅ በተመደቡበት የሥራ መስክ ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡

በመንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 መሠረት የመንግሥት ሰራተኞች መብትና ግዴታ ፣የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ኃላፊነት፣ የመንግሥት ሰራተኞች የስነ ምግባር ክስ እና ቅሬታ አቀራረብ ስርዓት እና በሙያ ስነ ምግባር ዙሪያ በንቃተ ሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ረዳት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ዮሐንስ አንዳርጌ ሥልጠናውን እየሰጡ ሲሆን በቀጣዩ ቀን ደግሞ የተቋሙ የሰው ሃብት ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ ተንኮሉ በተለያዩ ደንብ እና መመሪያዎች ዝርዝር የአሠራር አቅጣጫዎችን መሠረት ያደረገ ሥልጠና እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

ሥልጠናው በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን ቀጣይ ዙር ከሚያዚያ 9-10 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: administrative civil civil service law civil service regulations code of conduct employee employee training employees federal federal government employees Government Government Accountability government employees human resources management law legal Legal Training proclamation public sector training regulations Service staff Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች