ሰኔ 18/2016 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ መንግስቴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ህንፃ የዕድሳትና የግንባታ ስራ ያለበትን ሁኔታ በአካል ተገኝተው ገምግመዋል ፡፡
ግንባታውን አስመልክቶ ያለበትን የስራ እንቅስቃሴ ለዳይሬክተሩ በህንፃ ስራ ተቋራጩ በኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንና አበማካሪ ድርጅቱ ቺታ አማካሪ ድርጅት አማካኝነት ገለጻ ተደርጎላቸዋል፤ በስራው በኩል ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ስራውን አስመልክቶ በሁለቱ ድርጅቶች በኩል ስራው በታቀደለት የ8 ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ችግር እየሆነባቸው ያሉ ነገሮች አንስተዋል ፡፡-በዚህም የግንባታ ቁሳቁስ ማስቀመጫ ቦታ በፍርድ ቤቶች በኩል መከልከል ፣የፍትሕ አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ አለመነሳት፣የመብራት ትራንስፎርመርና የመብራት ፖል ቀድሞ ከቦታቸው አለመነሳት፣በቁፋሮ ወቅት ድንጋይ ማጋጠሙ እና የስራው ቅድመ ክፍያ መዘግየት መሆናቸውን አንስተው ተወያይባቸዋል፡፡
አቶ ደሳለኝ በጉብኝት ወቅት የህንፃ ዕድሳትና የግንባታ ስራ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑና የሰራተኞች የስራ መንፈስ መልካም መሆኑን ተናግረው በድርጅቶቹ በኩል እንደ ችግር የተነሱ ነጥቦችን በተቋሙ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ለችግሮች መፍትሔ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡
የህንፃው አፈፃፀምን በተመለከተ የግንባታው ሁኔታ 12.4% እና የፋይናንስ ሁኔታው 10.63 መድረሱ በገለፃው ተመላክቷል፡፡