የፍትህ ሚኒስቴር የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽንን የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ

Ministry of Justice Reviews the Federal Prison Administration Commission's 2016 Budget Year Performance Report

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽንን የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ገመገመ፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ወንድሙ የኮሚሽኑን የ2016 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርቱን አቅርበዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ ታራሚዎች ታርመው እና ታንፀው እንዲወጡ እየሰራቸው ያሉ ተግባራት የሚደነቅና ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አበክረው ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ኮሚሽኑ የሰራተኞችን ስነ-ምግባር የማጎልበት፣የማረም ማነጽ ስራን በማጠናከር እንዲሁም የውስጥ ደኅንነትና ጥበቃ ማጠናከር እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተው በስራ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊው ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል ክቡር አቶ የኑስ ሙሉ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ተገቢውን የሰው ኃይል፣ ቴክኖሎጂ እና ግብዓት በማሟላት ማረም ማነጽ ተሃድሶ ስራን ማዘመን እና የተቋሙን የጥበቃ ደኅንነት በማጠናከር ማረሚያ ቤቶችን የትምህርትና የምርት ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

Tagged Under: 2016 2016 budget year administration Budget commission correctional correctional services federal Federal Prison Administration Commission human resource development internal security performance Performance Review prison prison management prison reform reform Rehabilitation rehabilitation programs report resource allocation Services staff staff training Technology year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች