ፍትሕ ሚኒስቴር ከማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ጋር በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

Ministry of Justice and Prisons Commission Collaborating on Legal Awareness Education and Training

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ጉዳዮች ዙሪያ ከማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከማረሚያ ቤት ኮሚሽኑ ጋር ስራዎችን በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙንና በሰነዱ ከተካተቱ ጉዳዮች አንዱ ለማረሚያ ቤት ኮሚሽን ባለሙዎች እና ታራሚዎች ከንቃተ ሕግ ጋር የተያያዙ ሥልጠናዎችን መስጠት መሆኑን በሥልጠናው የመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ ናቸው።

ሥልጠናው የሚዳስሰው ታራሚን ማረም፣ ከህብረተሰቡ መልሶ መቀላቀል እና የሰብዓዊ መብት መከበር የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን እንደሆነ ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡ አያይዘውም የማረሚያ ቤት ስራ እጅጉን ከሰብዓዊ መብት ጋር የተቆራኘ መሆኑን በማውሳት በማረሚያ ቤት ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች የወንጀል ህጉን ዓላማ ለማሳካት ብሎም ግቡን እንዲመታ እና ታራሚዎች በሚፈለገው ልክ ታርመውና ታንጸው እንዲወጡ ለማስቻል ስራዎችን በጋራና በተቀናጀ መልኩ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የሥልጠናውም ዓላማ አዲስ ዕወቀት ማግኘት፣ ሰልጣኞች የእርስበርስ ልምድ መለዋወጥ እንዲችሉ ማድረግ እና ቀደም ሲል ሥልጠናውን ለወሰዱት ደግሞ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት የሚያስችል እንደሆነ አቶ እንዳልዛቸው ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሥልጠናው ተሳታፊዎች የስነ-ምግባርና ባህሪ ቀረጻ ባለሙያዎች፣ የታራሚዎች ፍትሕ አስተዳደር እና የታራሚዎች የፍትሕ ጉዳይ አስፈጻሚ ባለሙያዎች ሲሆኑ ሥልጠናው ለእነዚህ አካላት የስራ ሁኔታ አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ የሕግ ታራሚዎች ህጋዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው እና በሕግ ሊጠበቁላቸው እንደሚገባና ታራሚዎችን በአግባቡ አርሞ፣ አንጾ፣ ሰላማዊ፣ ሕግን እና የህብረተሰቡን ዕሴቶች የሚያከብሩ እንዲሆኑ ለማስቻል የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑን የገለጹት በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የተአድሶና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዝመራው አብደታ ናቸው፡፡ አክለውም ሥልጠናው የክህሎት ክፍተቶችንም የሚሞላ እንደሆነ አውስተዋል።

ሥልጠናው በንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዐቃቤያነ ሕግ አቶ መዝሙር ያሬድ እና አቶ ተሰማ ግደይ የሚሰጥ እንደሆነና በሥልጠናው የተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮችም ከሰልጣኞች የዕለት ተዕለት ስራቸው ጋር የተቀራኙ በመሆናቸው ሰልጣኞች ሥልጠናውን በትኩረት መከታተል እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: amhara region Awareness Capacity Building civil liberties correctional correctional services Criminal Justice Ethical conduct federal prison commission fundamental rights human Human Rights legal legal awareness training Legal Education offender rehabilitation prison prison reform prisoner prisons professional development reform Rehabilitation reintegration Rights Services Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች