በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ የተደረገውን ይህን የውይይት መድረክ የአስጀመሩት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽር ጄኔራል ዳመነ ዳሮታ እንደተናገሩት ረቂቅ ደንቦቹ ለመንግሥት ቀርበው እንዲጸድቁ ከመጠየቃችን በፊት አስፈለጊ ግብቶችን እና የማስተካከያ እርምት ሂደቶችን እንዲያልፉ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የካቤኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባን ጨምሮ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና የፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕግ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ረቂቅ ደንቦቹ በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ትቤሶ በዛብህ ቀርበዋል፡፡
ረቂቅ ደንቦቹ ከመጽደቃቸው በፊት በዘርፉ የካበት ዕውቀት እና ልምድ ባላቸው እና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢው አስተያየት ተሰጥቶባቸው እና ዳብረው እንዲያልፉ መደረጉ የኮሚሽኑን ስራዎች በሕግ ማእቀፎች ታግዞ ወጥ የሆነ ውጤታማ ስራ መሥራት የሚያስችለው እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ለውይይት የቀረቡ ሰነዶች የተሰጡ ግብቶችን በማካተት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ቀርበው ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡- የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፌስቡክ ገጽ