የፍትሕ ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዩች ዙሪያ ተወያዩ

Ministry of Justice Middle-Level Leaders Discuss Current National Issues

የፍትሕ ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮች “የህልም ጉልበት፤ ለዕምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዩች ዙሪያ ህዳር 10/2017 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፍትሕ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጐልተው ከሚነሱ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያዊያን የለውጥ ፍላጐትና ንቅናቄ መሆኑን አውስተው በትንሹ ባለፉት 7ዐ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ስለ ለውጥ መነጋገር፣ መጻፍ፣ አብዮት ማካሄድ፣ ግጭትና ግርግር መክፈት እና ከፍተኛ መሰዋዕትነት መክፈል የተለመዱ ህብረተሰባዊ ንቅናቄ ሆነው መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ ባለፉት አምስት ዓመታት እንደ ሀገር በርካታ ፈተናዎች ያጋጠሙ ቢሆንም እነዚህን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ፈተናዎች በመቋቋም በፖለቲካው ፣በኢኮኖሚው ፣በማኅበራዊና በዲፕሎማሲው ዘርፎች በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉን ክቡር አቶ ኡሞድ አክለው ገልፀዋል፡፡

በመቀጠልም በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ በክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ አማካኝነት “የህልም ጉልበት፤ ለዕምርታዊ እድገት ” በሚል መሪ ቃል ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን የያዘ የዳሰሳ ጽሑፍ ለተሳታፊዎች በዝርዝር ቀርቦ በቀረበው ጽሑፍ ላይ ውይይት በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: Economic development Political development
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች