የፍትሕ ሚኒስቴር የኦንላይን ይቅርታ መጠየቂያ ስርዓትን አስጀመረ

Ministry of Justice Launches Online Pardon Request System

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር በድሬዳዋ ማረሚያ ቤት በመገኘት የonline ይቅርታ መጠየቂያ ስርዓትን ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ/ም በድሬዳዋ ማረሚያ ቤት አስጀመረ፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ተወካይ፣ የተቋሙ የኢንፎሜሽን ቴክኖሎጂ መዝገብ አስተዳደር ዳይሬክተር እና የድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ኃላፊዎችና ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎች በድሬዳዋ ማረሚያ ቤት በመገኘት የonline ይቅርታ መጠየቂያ አገልግሎት ስርዓትን አስጀምረዋል፡፡

የሚኒስቴር ዴኤታው ተወካይ አቶ አማኑኤል ታደሰ ፕሮግራሙን ሲያስጀምሩ እንዳሉት የፍትሕ ስራ መገለጫው ስርዓቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን በማድረግ የተገልጋዮችን እንግልት የሚቀንስና እርካታን የሚጨምር እንዲሆን ማስቻል እንደሆነ አውስተዋል፡፡

አቶ አማኑኤል እንደገለጹት የፍትሕ ስርዓቱን ለማቀላጠፍና ለማዘመን በሦስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ አካቶ እየተሰራ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ተወካዩ አያይዘውም ከይቅርታና አመክሮ ጋር በተያያዘ ተገልጋዩ ማኅበረሰብ ባለበት ሆኖ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ እንደሚደረግ ገልጸው በቀጣይ በፍትሕ ሚኒስቴር እና በተጠሪ ተቋማት የሚሠጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የታገዙ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል፡፡

አቶ አማኑኤል ሲቀጥሉ ማረሚያ ቤቶች ከያዟቸው ታራሚዎች አንጻር መጀመሪያ ላይ ቃሊቲ በመቀጠል ዝዋይ አሁን ደግሞ ድሬዳዋ ማረሚያ ቤቶች የonline ይቅርታ ስርዓት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመላክተዋል፡፡

ተወካዩ በመጨረሻም የስርዓቱ መበልፀግ የተወሳሰቡ ስራዎችን ያስቀራል በማለት ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ዋና አስተዳዳሪ ኮሚሽነር ወንድሙ ደበላ ወቅቱ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ መሠረት አድርጋችሁ የይቅርታ መጠየቂያ ስርዓት ተጠቃሚ እንድንሆን ማስቻላችሁ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን አውስተው ሌሎችም ስራዎች በዚህ ቴክኖሎጂ ታግዘው መሰራት እንዳለባቸው ተናገረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም የonline የይቅርታ ማጠየቂያ ስርዐቱ በተቋማችን መጀመሩ አገልግሎቱን ፈልገው ወደኛ የሚመጡትን የታራሚ ቤተሰቦች እንግልትና የገንዘብ ወጪን የሚቀንስ ነው ብለዋል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የኢንፎሜሽን ቴክኖሎጂ መዝገብ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አማረ በገለጻቸው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የበላይ አመራሮች በተገኙበት ስርዓቱን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የይቅርታ መጠየቂያ ስርዓት ማስጀመራቸውን አውስተው ስርዓቱ በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በስራ ላይ ውሎ ውጤታማ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አቶ ፀጋዬ አክለውም አገልግሎቱ በኢትዮጵያ መንግሥት e-service ፖርታል ላይ የሚገኝ መሆኑን እና ስርዓቱ ቀላል የሚመስል ነገር ግን ፋይዳው ትልቅ እንደሆነ አውስተው ስራው በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

Tagged Under: amnesty application correctional correctional services dawa digital digital transformation dire E-Government Government Services kaliti prison online Pardon prison prison reform reform remission request Services system transformation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች