የወንጀል ፍትሕ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ በመልማት ላይ መሆኑ ተገለጸ

Development Of Technology To Digitalize The Criminal Justice System Is Underway, Officials Announced

የወንጀል ፍትሕ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ማድረግ የሚያስችል Criminal Records Information Management System (CRIMS) የተሰኘ ቴክኖሎጂ በመልማት ላይ መሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያስላሴ እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የአስተባባሪ ኮሚቴ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ስራቸውን የሚያከናውኑበትና ከወንጀል ጥቆማ ጀምሮ ምርመራ፣ ክስ፣ ክርክር እና ቅጣት ድረስ ያሉ ተግባራትን ዲጂታላይዝ አድርጎ በመመዝገብ መረጃዎችን መያዝ የሚያስችል ቴክኖሎጂ በመልማት ላይ መሆኑ በጋራ የአስተባባሪ ኮሚቴው የውይይት መድረክ ላይ ተወስቷል፡፡

በፍትሕ ዘርፍ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ሲሆኑ ከዚህም መካከል የወንጀል ፍትሕ ስርዓቱን ዲጂታል በማድረግ አሰራሩን ማዘመን የሚያስችል Criminal Records Information Management System (CRIMS} የተባለ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አማካኝነት በመልማት ላይ ነው።

ቴክኖሎጂው ወንጀል ተፈጽሞ ሪፖርት ከተደረገበት ቅጽበት ጀምሮ እስከ ማስቀጣት ደረጃ ድረስ ያሉትን ሂደቶች መረጃ አንድ በአንድ ሰብስቦ ለመያዝ የሚያስችል ከመሆኑ ሌላ፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ የሆነ መረጃ እንዲኖራቸው፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ የሰብዓዊ መብትን ለማስከበር፣ በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ለመዘርጋት የሚያስችል፣ የተመዘገቡትን መረጃዎችም ሚስጢራዊነታቸው ተጠብቆ እንዲቆዩ በማድረግ በወንጀል ፍትሕ ስርዓቱ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ መረጃ እንዲኖር የሚያደርግ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በመልማት ላይ የሚገኘው Criminal Records Information Management System (CRIMS} መረጃ ጥቆማ መቀበያ፣ ምርመራ፣ ወጣት ጥፋተኞች መረጃ፣ የወንጀል አይነት፣ Biometric data፣ የዐቃቤ ሕግ ውሳኔ፣ የፍርድ ውሳኔ እና ሌሎች መሰል ጉዳዮችን አካቶ በዲጂታል መልክ ለመያዝ የሚያስችል የወንጀል ፍትሕ ስርአቱን ከፍ ወደ አለ ደረጃ ማድረስ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ የወንጀል ፍትሕ ስርዓቱን አውቶሜት በማድረግ የወንጀል ምርመራ እና ክስ አሰራር ስርዓታችንን ማሻሻል፣ ፈጣንና ውጤታማ የሆነ አገልግሎትን መስጠት፣ አሁን ባለው መደበኛ አሰራር ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት፣ ለተገልጋዮች ፈጣን ምላሽ የመስጠት ውስንነቶችን መቅረፍ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራን መፍጠር፣ የተሻለ ቅንጅታዊ አሰራርን በተቋማት መካከል መዘርጋት እንዲሁም በቀጣይነት በዘርፉ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን በትክክል መለየት የሚያስችል እና የለፖሊሲ ውሳኔ ግብዓት የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Tagged Under: age ali criminal Criminal Justice Criminal Justice System criminal record crims data data management system development digital formation information Information management information management system information technology management iom Justice Justice System management management information system (mis) official officials record records records management system system Technology un way
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች