በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ከአዲስ መሶብ አገልግሎት ጋር በቅንጅት በሚሰራባቸው ጉዳዩች ላይ ከተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ጋር ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ተወያይተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በአዲስ መሶብ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የማዕከሉን የሥራ ዕንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን፤ በዚህም ወቅት የተቋሙ ዋና ዳይሬክቴር አቶ ዮናስ አለማየሁ የማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ ገለፃ ሰጥተዋል፡፡
ፍትሕ ሚኒስቴር በተለይም የጥብቅና ሙያ እና አገልግሎት እንዲጎለብት ለማድረግ የጥብቅና የሙያ ፈቃድ ከመስጠት እና ከማደስ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን በአዲስ መሶብ አገልግሎት ማዕከል ስር በማቀፍ አገልግሎቱን ቀልጣፋና ተደራሽ በሆነ መልኩ ለመስጠት አስቻይ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ክቡር አቶ በላይሁን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም ከጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ማዕከሉ ማካተት የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች በማንሳት ውይይት አድርገዋል፡፡