የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት 22ኛውን የፀረ- ሙስና ቀን አከበሩ

Ministry of Justice alongside its accountable institutions, officially commemorated the 22nd International Anti-Corruption Day

የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ”ትውልድን በሥነ- ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር ”በሚል መሪ ቃል 22ኛውን የፀረ- ሙስና ቀን የተቋማቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች በተገኙበት ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡

ይህንን ቀን “ትውልድን በሥነ -ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል ስናከብር ትውልድን በሥነ -ምግባር ሲባል እያዳንዳችን በተሰጠን ኃላፊነት ስነ-ምግባራዊ አገልግሎት እየሰጠን መሆናችንን ለማስታወስ ሲሆን፤ ተቋምን በአሰራር ስንል ደግሞ ሙስናን የመዋጋት ስራዎቻችን ፍሬ እንዲኖራቸው የተቋሞቻችንን አሰራር መፈተሸ ስንችል እንደሆነ ማሳያ መሆኑ ተገልጿል ፡፡

እንደ ፍትሕ ሚኒስቴር ከውስጥ ተቋማዊ ስነ-ምግባርን ከማረጋገጥ ባለፈ ሙስናን ጨምሮ አጠቃላይ የወንጀል ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ይህንን ቀን ስናከብር በውስጥ እይታ ግልፅነት እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንዲሁም አጠቃላይ በፍትሕ ስርዓቱ ውስጥ ያሉትን የተጠያቂነት ስርዓትን ማረጋገጥ ትልቁ ስራችን በመሆኑ በትጋት እየሰራን ሙስናን መዋጋት ላይ ቁልፍ ሚና እንዳለው ተቋም ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

በመድረኩ የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ጠቋማት ከፍተኛ አመራሮች የሀብት ምዝገባ ርክክብ ያካሄዱ ሲሆን ይህንን ተከትሎም በፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ የንቅናቄ ሰነድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱም የፀረ ሙስና ቀን ሲከበር በዓመት አንዴ ከሚደረግ መርሃ-ግብር ባለፈ በቤታችን ሙስናን የሚፀየፍና በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራት ላይ እንዲሁም በየተቋሞቻችን ግልፅ የሆኑ ስርዓቶችን መዘርጋት እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ በኩል ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም የፍትሕ ዘርፍ ፎረም የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክፍሎች ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

Tagged Under: account • african charter on the rights and welfare of the child • Anti-Corruption • convention on the elimination of all forms of discrimination against women (cedaw) • Convention on the Rights of the Child • convention on the rights of the child (crc) • Corruption • day • ethiopian federal ministry of justice • Ethiopian Ministry of Justice • fdre ministry of justice • federal ministry of justice • institution • institutions • international • international criminal justice • international criminal justice cooperation • International Women's Day • itu • Justice • justice for all • Justice For All - PF Ethiopia • ministry • National • official • rate • un
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች