የብሔራዊ እና የክልል የትብብር ጥምረት አደረጃጀቶች የ2014 የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም የጋራ መድረክ ተካሄደ

Joint Forum on Federal and Regional Cooperation Mechanisms Mid-Year Plan Performance 2014

የብሔራዊ እና የክልል የትብብር ጥምረቶች የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄድ፡፡

የአፈጻጸም ግምገማ መድረኩን በንግግራቸው ያስጀመሩት በፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትህያ ሰዒድ አንደተናገሩት ይህ መድረክ በፌዴራል እና በክልሎች የትብብር ጥምረቶች ባለፈው ስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሂደት ውስጥ ዕቅዳችንን ስንፈጽም የነበሩንን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች በመመልከት ለቀጣይ ስራዎቻችን ስንቅ ሆኖ የሚያገለግል የጋራ አቅጣጫ በመያዝ ወደ ስራ ስለምንገባበት ሁኔታ የምንመክርበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡

በመቀጠልም የትብብር ጥምረቱ ጽ/ቤት፣ በብሔራዊ ትብብር ጥምረቱ ስር የተደራጁት ስድስት የስራ ቡድኖች እንዲሁም የክልሎች የትብብር ጥምረቶች የ6 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶቻቸውን በተወካዮች አማካይነት አቅርበዋል፤ በቀረቡር ሪፖርቶች በተነሱ አንኳር ጉዳዮችም ላይ ከቤቱ በተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶል፡፡

በመጨረሻም በቀጣይ ትኩረት ቢደረግባቸው ተብሎ በተለዩ ጉዳዮች ላይ በጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር ተመስርቶ ቀጣይ ቀሪ የበጀት ዓመቱ ወራት ዕቅዶች በሚከናወኑባቸው ሁኔታዎች ላይ በመስማማት ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው መድረክ ተጠናቋል፡፡

Relevant Departments and People
Tagged Under: Joint Forum Policy Implementation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች