የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በሚዛን አማን ከተማ በመገኘት የሚዛን አማን ማረሚያ ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉበኝቱም ወቅት የፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን እና የትራንስፎርሜሽን ግብረ ኃይል አባላት ተገኝተዋል፡፡ በዚህ ጉብኝት የታራሚዎች አያያዝ እና አጠባበቅ ምን እንደሚመስል ምልከታ አድርገዋል፡፡ ከዚህ በማስከተልም በማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በአገር ዓቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ መሠረት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አከናውነዋል፡፡