በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከልና የፍልሰት አስተዳደርን ለማሻሻል ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በመገምገም ሀገራዊ አቅሞችን ማሳደግ እንዲገባ ተገለፀ

It was announced that domestic capacity should be enhanced by evaluating international situations in order to prevent the crimes of human trafficking and human smuggling across borders, and to improve migration management.

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከአለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM) እንዲሁም ከአለማቀፉ የፃናት አድን ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የብሔራዊ ትብብር ጥምረት መድረክ በሁለተኛ ቀን ውሎው በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን መከላከል፤ በምክር ቤቱ የተሰጡ አቅጣጫዎች እና የፍልሰት አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የትኩረት መስኮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ብሔራዊ ትብብር ጥምረት የምክር ቤቱ ከሰጣቸው አቅጣጫዎች መካከል በተለይም መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ለዜጎች ጥበቃና ድጋፍ ለማድረግ የመንግስትና የፖለቲካ ቁርጠኝነትን ማሳደግ፤ የሀገር ውስጥ ሥራ እድል ፈጠራ ማጠናከር፤ የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አመራርን በማሻሻል ዜጎች መደበኛው መንገድ አማራጮችን እንዲከተሉ ማድረግና አዳዲስ የመዳረሻ ሀገራትን ማስፋት፤ በኤጀንሲዎች ላይ ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ፤ የህግ ማስከበር እርምጃዎችን ማጠናከር፤ ኢንተሊጀንስን መሰረት በማድረግ አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑና የወንጀል ፍሬዎች እንዲወረሱ ማድረግ፤ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር፤ የድንበር ቁጥጥርን ማጠናከርና ቅንጅትን ማጎልበት፤

ወንጀሎችን ለመከላከልና የፍልሰት አስተዳደርን ለማሻሻል ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በመገምገም ሀገራዊ አቅሞችን ማሳደግ፤ የፖሊሲ፣ የሕግና የትብብር አደረጃጀቶች በፌደራልና በክልል እንዲጠናከሩ ማድረግ፤ ከተመላሾች ቅብብሎሽና መልሶ ማቋቋም ጋር በተያያዘ በሕግ በተቀመጠው አግባብ የተዘረጉ የአሰራር ሥርዓቶችን ተከትሎ ተጠያቂነት ባለበት መልኩ ተግባራዊ ማድረግ፤ በትብብርና በቅንጅታዊ አደረጃጀቶች ውስጥ የተጠናከረ የተጠያቂነት ሥርዓት መዘርጋት የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡

በ2018 በጀት ዓመትም ግንዛቤ ፈጠራ ፤ የተጎጂዎች ድጋፍና መልሶ ማቋቋም፤ መደበኛ የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት፤ የሕግ ማስከበርና ድንበር አስተዳደር፤ የፍልሰት መረጃና ምርምር፤ የዳያስፖራ ተሳትፎና ልማት ፤ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና ሕጎች ፤ ድጋፍ፣ ክትትልና ተጠያቂነት የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ በዘርፉ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም ባለፈው ዓመት በ2018 ዓመት ውጤት ለማምጣት መሰረት የሚሆኑ ሥራዎች መከናወናቸው የተወሳ ሲሆን፤ በቀጣይም አዳዲስ የተቋቋሙ ቡድኖች ወደ ሥራ ከማስገባት ጋር፤ ክልልሎች ህጎችና ደንቦችን እንዲያወጡ ከማድረግ እንዲሁም አደረጃጀቶችን ከመፍጠር፤ የፀደቀውን የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ተግባራዊ ከማድረግና፤ የእያንዳንዱን የሥራ ቡድን እንቅስቃሴዎች በየጊዜው ከመገምገም ጋር የተያያዙ መሰረታዊ የሆኑ ሥራዎች ላይ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ በመድረኩ ማጠቃለያ ወቅት ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: african charter on the rights and welfare of the child age border capacity city Crime Crimes cross domestic event human human smuggling Human Trafficking international international organization for migration (iom) iom itu management Migration Migration Management National order pro ratio Smuggling traffic trafficking un
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች