ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ በፍልሰት አስተዳደር አብረዉ ለመስራት በሚያስችሏቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

Ethiopia and Mozambique Discuss Cooperation on Migration Management

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርሚያስ የማነብርሃን(ዶ/ር) ከየሞዛምቢክ የማይግሬሽንና የኢሚግሬሽን አገልግሎት ዋና ኮሚሽነር ክቡር ዜናዳይን ጆ ዳናኒ (zainadine joao Danane ) እና ልዑክ ቡድናቸው ጋር ሚያዝያ 19/08/2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ በፍልሰት አስተዳደር ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ዉይይት አድርገዋል፡፡

በዉይይቱ ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ለበርካታ አመታት የዘለቀ አብሮ የመስራት ልምድ እንዳላቸዉ የተነሳ ሲሆን፤ ይህንን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር በተለይም በፍልሰት ዙሪያ አብረዉ ለመስራት ያላቸዉን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

መደበኛ ባልሆነዉ ፍልሰት በሚደረግ እንቅስቃሴ ሞዛምቢክ መተላለፊያ አገር መሆኗንና ለዚህም የተጠናከረ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደሚያስፈልግ የገለፁት ክቡር ኤርሚያስ የማነብርሃን(ዶ/ር) በተለይም በፍልሰት አስተዳደር፤የተጎጂዎች ድጋፍ ፣ጥበቃና ወደ አገራቸዉ በክብር መመለስ ላይ፤ በህግ ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብርና በመሰል ጉዳዮች ላይ የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ አክለዋል፡፡

ክቡር ዜናዳይን ጆ ዳናኒ በበኩላቸዉ የፍልሰት አስተዳደርን በሚመለከት ሞዛምቢክ ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀዉ መደበኛ ባልሆነ ፍልሰትም ሆነ በሌሎች መሰል ጉዳዮች አህጉራዊ የሆነ ለዉጥ ለማምጣት ያስችል ዘንድ ሁሉም የአፍሪካ አገራት በጋራ በመሆን የመወያየት እና ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ሁለቱ አገራት በቀጣይ ቁልፍ የሆኑ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት እና የስራ መዘርዝሮች የተካተቱበት በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራ የጋራ ስምምነት ሰነድ ለማዘጋጀት ያስችላቸዉ ዘንድ የጋራ ቴክኒካል ቡድን በማቋቋምና ዉይይቶችን በማድረግ በቅርቡ ስምምነቱን ተፈራርመዉ ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልፀዋል።

Tagged Under: account management adama science and technology university Addis Ababa Science and Technology University addis ababa water and sewerage authority african charter on human and peoples’ rights african charter on the rights and welfare of the child african commission on human and peoples' rights age age of criminal responsibility agricultural cooperation and cultural rights and healthcare administration and control authority Cooperation ethiopia revenue and customs authority management medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 Migration Migration Management ministry of finance and economic cooperation mozambique national migration cooperation coordination office operation per ratio science and technology cooperation technical and vocational education and training technical and vocational education and training (tvet)
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች