በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና ከተማ በሰዉ የመነገድ ወንጀልን በመከላከልና በዳያስፖራ ተሳትፎ ዙሪያ የሚመክር የከፍተኛ አመራሮች የዉይይት መድረክ ተካሄደ

High-Level Officials Meet In Hosanna, Central Ethiopia, To Discuss Combating Human Trafficking And Diaspora Participation

የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጋራ ያዘጋጁት በሰዉ የመነገድ ወንጀልን በመከላከል እና በዳያስፖራ ተሳትፎ ዙሪያ የሚመክር የከፍተኛ አመራሮች የዉይይት መድረክ በክልሉ መቀመጫ ሆሳዕና ከተማ ለሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በሆሳዕና ከተማ ባለፉት ዓመታት በዳያስፖራዎች የተሠሩ የልማት ሥራዎችንም የመስክ ምልከታ ማድረግ ተችሏል፡፡

የዉይይቱ ዋና ዓላማ በተለይም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣዉን በሰዉ መነገድ እና በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችን በመከላከል እና በመቆጣጠር በህገወጥ መንገድ የሚደረገዉን ፍልሰት በመቀነስና ሕጋዊ ማዕቀፎችን በማጠናከር ፍልሰትን ለአገራዊ ልማት ለማዋል እና የዳያስፖራዉን ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በክፍተኛ አመራሮቹ የዉይይት መድረክ ላይ በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋን ጨምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የክልልና ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ባንኮች የተገኙ ሲሆን በናይሮቢ፣ ዳሬሰላም እና ሐራሬ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጭምር በበይነ-መረብ የዉይይቱ ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ፣ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ከዓለም ዓቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት እና በደቡብ ንፍቀ ክበብ የፍልሰት መንስኤዎች ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ለፓናል ዉይይቱ መነሻ የሚሆኑ ጥናቶችን ያቀረቡ ሲሆን በዉይይቱ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በቀጣይ ለፍልሰት ገፊ ምክንያቶችን በመለየትና ችግሮችን ከሥር መሠረታቸዉ በመፍታት፡አደረጃጀቶችን በማጠናከር፡ የመልሶ ማቋቋም ሥራችንን በመገምገም፡ ከአገራት ጋር ያለንን የሆለትዮሽ ግንኙነት እና በደቡብ ንፍቀ ክበብ ከሚገኙ የኢትዮጵ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር የተጠናከረ ሥራ መሥራት እንደሚገባ በክቡር ሚኒስትር ዲኤታዉ አቶ በላይሁን ይርጋ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን፣ ዉይይቱ እንዲሳካ የፋይናንስ ድጋፍ ያደረጉትን ጂ.አይ.ዜድ እና ሴቭ ዘ ቺልድረን ዕዉቅና ተሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች የክልሉ የዳያስፖራ ኢንቨስትመንት ቢሮ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ምክንያት ከሃገር ወጥተው የነበሩና ተመላሽ የሆኑ ዜጎችን በማደራጀት ባደረገው ድጋፍ በእንሰሳት እርባታ፤ በንብ ማነብ እና በዕርሻ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን እንዲሁም በሆቴል አገልግሎት እና በኢንዱስትሪ ልማት ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ዳያስፖራዎችን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

Tagged Under: adama science and technology university african charter on human and peoples’ rights african commission on human and peoples' rights and healthcare administration and control authority Business and Human Rights central central bank of ethiopia combating combating human trafficking diaspora ethiopia human rights commission ethiopia revenue and customs authority high high-level human Human Trafficking human trafficking prevention level medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 ministry of public service and human resource development official officials participation technical and vocational education and training technical and vocational education and training (tvet) traffic trafficking un guiding principles on business and human rights un high commissioner for human rights
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች