የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

First-Quarter 2018 Performance of Institutional Building and Reform Division Reviewed

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ ቀርቦ የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃን እንዲሁም በዘርፉ በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡

በዘርፉ በተለይም የፕሮጀክት ሥራዎችን በተመለከተ፤ የክትትልና ግምገማ ሥርአት ከመዘርጋ፣ ከመምራትና ከማስፈፀም ጋር በተያያዘ፤ የሰው ሃይል ልማት ውጤታማትን ከማሳደግ፤ የሃብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ከማሳደግ፤ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ከማሳደግ፤ ከትብብርና ቅንጅታዊ ሥራ ጋር በተያያዘ፤ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክትትል ሥራዎችን በተመለከተ ፤የሴቶችና ማህበራዊ ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ከማሻሻል፤ ከወንጀል ፍትሕ አገልግሎት እንዲሁም የህብረተሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎትን ከማሳደግ አኳያ የተሰሩ ሥራዎች በሪፖርቱ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

የፕሮጀክት ስራዎች በተመለከተ ለአብነት የዋናው መስሪያ ቤት የነበረ ግንባታና የማስፋፊያ ስራን ማካሄድ፣የልደታ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሕንጻ ማጠናቀቅ፣የጉለሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ህንፃ መገንቢያ ቦታን የመረከብ ሥራዎች መከናወናቸው ተመላክቷል፡፡

የሰው ሃብት ልማት ውጤታማነትን ከማሳደግ አኳያ እንዲሁ የዐቃቤያነ ሕግ የአለባበስ ገጽታ መመሪያ ወደ ትግበራ እንዲገባ የተደረገበት፣ የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ጋር መረጃ የማደራጀት እና የማስመዝገብ ስራ እን የዐቃቤያነ ሕግ የአፈጻጸም ምዘና ተግባራዊ መደረጉ እና የትምህርት እድል በውጭና በአገር ውስጥ ለሠራተኛው መሰጠቱ በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡

በስልጠና ረገድም ፍላጎቶችን መሠረት ያደረጉና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳየች ላይ ያተኮሩ ስልጠኛዎች በገፅ ለገፅ እንዲሁም የE-Learning ዘዴን በመጠቀም መስጠት የተቻለ ሲሆን፤ የኢንፎርሜሽን ቴጀክኖሎጂን ከማሳደግ አንጻርም በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የተቋሙን ዌብሳይት ጨርሶ ለአገልግሎት ማብቃት እንዲሁም በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ወንጀል፣ የሴቶችና ህፃናት የወንጀል የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት በልፅጎ በሙከራ ላይ እንዲውል ማድረግ መቻሉ ተገልፆል፡፡

የትብብር እና ቅንጅታዊ አሰራርን ከማሳደግ ጋር በተያያዘ እንዲሁ ከፌዴራል እና ክልል አጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት በተለያየ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን መስጠት መቻሉን፤ የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮ የጋራ ጉባኤ ማካሄድ መቻሉ፤ በስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ጥቆማዎችን ተቀብሎ ተገቢ ክትትል የማድረግ፤ የሴቶችና ማህበራዊ ተሳትፎ ተጠቃሚነትን በሚመለከትም ሥልጠና በመስጠት አቅም የመገንባት ስራ መከናወኑ፤ በማቆያና በአንድ ማዕከል አገልግሎት ክትትል መደረጉ፤ ከአፋርና ሶማሌ ክልሎች ጋር በመቀናጀት የቤተሰብ ህግ እንዲዘጋጅ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

በመጨረሻም በቀረበው 1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እንዲሁም የዘርፍና የሥራ ክፍሎች የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረ ሲሆን፤ በዚህም መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮችን በቀጣይ እየፈቱ የጎደሉ ነገሮች በማሟላት መቀጠል እንደሚገባና በስትራቴክ እቅዱ የተቀመጡ ተግባራትን በሚመለከት ግልፅነትን በማስፈን ለሰራተኛው በዝርዝር የሚያከናውናቸውን ተግባራት ቆጥሮ በመስጠት ዉጤት ላይ ያተኮረ ስራን ለመፈፀም ሁሉም ሰው መረባረብ እንደሚጠበቅበት አቅጣጫ ተሰጥቶ የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: academic and healthcare administration and control authority appeal arra (agency for refugees and returnees affairs) budget performance review building Capacity Building court division e-learning Education first first quarter performance review institution institutional itu judiciary learning per performance quarter reform review school skill development Training vision
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች