የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያውን ተከትሎ አዲስ በወጡና በተሻሻሉ ሕጎች አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

Discussion Held on the Implementation of New and Amended Laws Following Justice System Reform

የውይይቱ ዋንኛ ትኩረት ለዉጡን ተከትሎ ተግባራዊ ከተደረጉ የሕግ ሪፎርም ስራዎች ጋር ተያይዞ አዲስ በወጡና በተሻሻሉ ሕጎች በተለይም የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ፣ የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ፣ የፌዴራል ጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ እንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ አፈጻጸም ጋር በተገናኘ በጥናት በተለዩ ክፍቶችና መወሰድ በሚገባቸው የመፍትሄ እርምጃዎች ዙሪያ፣ ከባልርሻ አካላት ጋር መምከርና ከመድረኩ ተሳታፊዎች የሚሰጡ መክረ ሃሳቦችን ተቀበሎ የጥናቱ አካል በማድረግ ለአተገባበሩ ዉጤታማነት የጋራ ግንዛቤ መያዝ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት፣ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር፣ የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒሰትር ዴዔታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰገድ አያሌው ሲሆኑ፣ ባለፉት አራት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የፍትሕ ዘርፉን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሪፎርም ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፤ በመሰራትም ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በለውጡ ሂደት፣ በተለይም የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ እና በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ፣ በርካታ የሕግ ማዕቀፎች እንዲሻሻሉ አልያም በአዲስ መልክ ወጥተው ስራ ላይ እንዲውሉ የተደርገ መሆኑን የገለጹት የጽ/ቤት ኃላፊው፣ አዋጆቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከተደረገ ጊዜ ጀምሮ ያላቸው የአፈፃፀም ሂደት እና የተመዘገቡ ውጤቶችን ለመለየት እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን ነቀሶ በማውጣ የመፍትሔ ሀሳቦችን ለማስቀመጥ እንዲያስችል ከተለያዩ አካላት የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የጥናት ቡድን ተዋቅሮ በአዋጆቹ አፈፃፀም ላይ የዳሰሳ ጥናት ሰለመረጉ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ የዳሰሳ ጥናት ግኝቶቹ፣ በተለያዩ የጥናት ቡድን አባላት በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ አዋጆቹ ስራ ላይ በመዋላቸው ምክንያት አንደ ሀገር ያስገኙዋቸው በርካታ ትሩፋቶች እንደተሰተዋሉ ሁሉ በአተገባበር ወቀት የታዩና ማስተካከያ የሚሹ የሕግና የአፈጻጸም ከፍተቶችም በዳሰሳ ጥናቱ ስለመለየታቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም፣ ችግሮቹን ለመቅረፍ፣ ከሕግና አፈጻጸም አንጻር ከፍተት የተስተዋለባቸውን ድንጋጌዎች ከማሻሻል ጀምሮ ለማህበረሰቡና ለፍትሕ አካላት ማለትም ለዳኞች፣ ለዐቃቤያነ ሕግ፣ መዝጋቢና መርማሪ ፖሊሶች ሥልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት፣ የተቋማትን አቅም በሰው ኃይልና በግብዓት መገንባት፣ ወይም ማሳደግ፣ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንዲሁም ተከታታይ ውይይቶች እንዲካሄዱና የአፈጻጸም ሪፖርቶች በየወቅቱ እንዲቀርቡ ክትትል ማድረግ በጥናቶቹ ከተጠቀሱ ምክረ ሃሳቦች መካከል ዋንኛዎቹ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በውይይቱ ተሳታፊዎች ጠቃሚ የሆኑ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን የጥናት ቡድን አባላቱም የተሰጡ አስተያየቶችን በግብዓትነት በመውሰድ ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራርያና ምላሽ የሰጡ ሲሆን በአዋጆቹ አተገባበር ዙሪያም ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

Tagged Under: administrative Administrative Procedure Amhara Regional State Capacity Building control counter-terrorism legislation court federal federal supreme court firearms firearms control Implementation Justice Justice System Reform law legal Legal Frameworks Legal Gaps Legal Reform licensing regulations Performance Evaluation Policy Implementation policy recommendations procedure reform stakeholder consultations supreme system training programs
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች