በሰዎች የመነገድ ወንጀል ክስ አመሰራረት ጋር ተያይዞ ባሉ ውስንነቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተዘጋጀ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ውይይት ተደረገ

Discussion Held on Research Paper Addressing Gaps in Human Trafficking Case Adjudication

በሰዎች የመነገድ ወንጀል ክስ አመሰራረት ጋር ተያይዞ ባሉ ውስንነቶች ላይ ዳኞች፣ ዐቃቤ ህጎች፣ መርማሪ ፖሊሶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ጥናት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሊሻሻሉ በሚገባቸው ጉዳዮች መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

የጥናታዊ ጽሑፉን መቅረብ አስመልክቶ በሰዎች የመነገድ ወንጀል ጋር በተያያዘ እየተከናወነ ባለና መከናወን በሚገባው ሂደት ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት በፍህ ሚንስቴር የብሔራዊ ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግ አቤል ገብረእግዛብሔር እንደተናገሩት ሀገራችን የፍልሰተኞች መነሻና መዳረሻ አገር እንደመሆኗ በዜጎች ላይ በርካታ ችግሮች እየተፈጠሩ እንዳለ ገልጸው ችግሩን ከመከላከል አንጻር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነና ችግሮች ከተከሰቱ በኋላ አጥፊ አካላትን ከማስቀጣትና ተጎጆዎችን መልሶ ከማቋቋም አኳያም ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ከችግሩ ውስብስብነትና አሳሳቢነት አንጻር ቅንጅታዊ አሠራርን በጉልህ የሚፈልግ ተግባር እንደመሆኑም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ የገለጹት ዐቃቤ ህጉ ተቋሙ የብሔራዊ ፍልሰት ትብብር ጥምረት ተግባርን የመከታተልና መቆጣጣር ስራውን በተጠናከረ መልኩ እየተገበረ ቢሆንም አሁንም በሚፈለገው ደረጃ ችሩን መቀነስ ያልተቻለ በመሆኑ ጥናት ማድረግ እንዳስፈለገ ተናግረዋል፡፡

አክለውም በሰዎች የመነገድ ወንጀል ከመከላከል እና ሕግ ከማስከበር ጋር ተያይዞ በ2013 ዓ.ም የክልሎች አፈጻጸም ባጭሩ ምን እንደሚመስል አቅርበው ከችግሩ ጉልህነት አንጻር በቀጣይ ከዚህ የበለጠ አትኩሮትን የሚሻ በመሆኑ ማኅበረሰብ አቀፍ የመከላከል ስራ መሥራትና ቅንጅታዊ አሠራርን የበለጠ ማጠናከር ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ጥናታዊ ጽሁፉን ያቀረቡት ከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር ታደሰ ስሜ በሰዎች የመነገድ ወንጀል ክስ አመሰራረት ጋር በተያያዘ የተገኙ ውስንነቶችና ከሕግና አፈጻጸሙ ጋር ያሉ ክፍተቶችን የዳሰሰ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ዳኞች፣ ዐቃቤ ህጎች፣ መርማሪ ፖሊሶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ጥናቱ ቀርቦ ሊሻሻሉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Relevant Departments and People
Tagged Under: Human Trafficking • Justice • Research
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች