በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ፍትሕ ሚኒስቴር የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ጉዳይ መከታተያ ዳይሬክቶሬት ቀደም ሲል ከነበረበት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቫርኔሮ አዳባባይ አካባቢ የሚገኘው የፍትሕ ሚኒስቴር ሕንፃ ከ04/06/2016 ዓ/ም ጀምሮ ልደታ ወደሚገኘው የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ የተዛወረ በመሆኑ ተገልጋዮች ሀዋሳ እና ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የሚገኙ የፍትሕ ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በሚሰጧቸው ውሳኔዎች ላይ ለሚኖራችሁ ቅሬታ ወይም አቤቱታ አዲስ ወደተዛወረው ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በኦንላይን www.eservice.gov.et በመጠቀም ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴር