•
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ) ፍትሕ ሚኒስቴር፤ የፍትሕ ዘርፉን የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የህብረተሰቡን ፍትሕ የማግኘት መብት ማስከበር፤ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፤ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ማክበርና ማስከበር፤ የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር፤ የወንጀል ሕጎችንና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ፖሊሲውን ማስፈጸም፤ የፌዴራል መንግሥት ያወጣቸውን ሕጎች ተፈጻሚነት ማረጋገጥ፤ የምስክሮችና የጠቋሚዎች ጥበቃና ከለላ አዋጅን ማስፈጸም፤ የፌዴራል መንግሥት በሚያወጣቸው ሕጎች፣ በሚወስናቸው ውሳኔዎችና ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የማማከር፤ የፌዴራል መንግሥቱንና የሕዝብን ፍትሐ ብሔራዊ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ፤ እንዲሁም በወንጀል የተገኘ ሀብትን የማስመለስ ተልዕኮ ተሰጥቶታል።
ተቋሙ ይህንን ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራር በመቅረጽ፣ ሕዝብና መንግሥት ከፍትሕ ዘርፍ የሚጠብቁትን ውጤት ለማሳካት ባለፈው የስትራቴጂክ ዕቅድ ዘመን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ውጤቶችን አስመዝግቧል።
ስለሆነም በተቋሙ ኃላፊነቶች አፈጻጸም ዙሪያ የሚታዩ አንኳር ክፍተቶችን ለይቶ ለመቅረፍ፣ በተቋሙ የተጀመረውን የሕግና ፍትሕ ሪፎርም በማስቀጠል የተገኙትን ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ማውጣትና መተግበር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ስትራቴጂያዊ አመራር መስጠት የሚጠይቅ በመሆኑ፣ የተቋሙ የአሥር ዓመት መሪ ዕቅድ እንዲሁም የአምስት ዓመትና የሦስት ዓመት ዝርዝር ስትራቴጂክ ዕቅዶች ተዘጋጅተው ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ እነዚህም ዕቅዶች ለዓመታዊ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት እንደ መነሻ ያገለግላሉ፡፡
ሆኖም የፍትሕ ዘርፉ ሕዝብና መንግሥት የሚጠብቁትን ውጤት ከማስመዝገብ አንጻር በርካታ ጉድለቶች የሚስተዋሉበት መሆኑን፤ ያለፉት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማዎች፣ በተለያዩ መድረኮች ከሕብረተሰብ ተወካዮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረጉ ውይይቶች፣ እንዲሁም መንግሥት የፍትሕ ዘርፉን ተቋማዊ ቁመና በዝርዝር በገመገመበት ወቅት ችግሮች ያሉበት ስለመሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የሦስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን የመንገድ ካርታ (roadmap) ተዘጋጅቷል። በዚህ የመንገድ ካርታ ላይ ስለዘርፉ ክፍተቶች በርካታ ጉዳዮች ተካተዋል፡፡ በተጨማሪም ፍትሕ ሚኒስቴር ይህንን ችግር የሚቀርፍ ሪፎርም ለመምራት የሚያስችል የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ አደራጅቷል፡፡
ከላይ ከተገለጹት የረጅም እና የመካከለኛ ጊዜ ስትራቴጂክ ዕቅዶች በመነሳት በ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሚተገበሩ ግቦችንና ዋና ዋና ተግባራትን የሚያመለክት ይህ መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቷል። መሪ ዕቅዱ በሰባት ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡ ይኸውም፦
•
•