•
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የፍትህ ዘርፉን የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የህብረተሰቡን ፍትሕ የማግኘት መብት በማስከበር የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ ህገ መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን የማክበርና የማስከበር፣ የዜጎች ሰብአዊ ዴሞክራሲዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር፤ የወንጀል ህጎችንና የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ፖሊሲውን የማስፈጸም፣ የፌዴራል መንግስት ያወጣቸውን ህጎች ተፈፃሚነት ማረጋገጥ፤ የምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃና ከለላ አዋጅ የማስፈፀም፤ የፌዴራል መንግስት የሚያወጣቸውን ህጎች፣ የሚወስነውን ትላልቅ ውሳኔዎችና ብሄራዊ ጥቅምን የሚመለከቱ ግንኙነቶችን የማማከር፤ የፌዴራል መንግስቱንና የሕዝብን ፍትሐብሄራዊ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ እና በወ/ል የተገኘ ሀብት ማስመለስ እንዲሁም ሠነዶችን አረጋግጦ መመዝገብ፣ የሲቭል ማህበራት ድርጅቶችን ክትትል፣ ግገማና ምርመራማድረግ፣
የግብር ይግባኝ ጉዳዮችን አከራክሮ መወሰን እና የህግ ታራሚዎችን የማረምና የማነፅ አገልግሎት ተልዕኮዎች ተሰጥተዋል፡፡ እነዚህን ተልእኮዎች ለመወጣት አደረጃጀትና አሰራር በመቅረጽ ሕዝብና መንግሥት ከፍትሕ ዘርፉ የሚጠብቁትን ውጤት ለማሳካት ባለፈው እስትራቴጂክ የዕቅድ ዘመን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ስለሆነም በፍትህ ዘርፉ ሃላፊነቶች ዙሪያ የሚታዩ አንኳር ክፍተቶችን ለይቶ ለመቅረፍ እና በተቋሙ በተጀመረው የሕግና ፍትሕ ሪፎርም የተገኙትን ውጤቶች
ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የረጅም ጊዜ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ
በማውጣትና በመተግበር እስትራቴጅያዊ አመራር መስጠት የሚጠይቅ በመሆኑ
የፍትህ ዘርፉን የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ እና አምስት ዓመታት ዝርዝር እስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቶ እየተሰራበት ሲሆን ለሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱ እንደመነሻ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ሆኖም የፍትህ ዘርፉ ሕዝብና መንግስት የሚጠብቁትን ውጤት ከማስመዝገብ አንፃር በርካታ ጉድለቶች የሚስተዋሉበት መሆኑን ያለፉት የእቅድ አፈፃፀም
ግምገማዎች እና በተለያዩ መድረኮች ከሕብረተሰብ ተወካዮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረጉ ውይይቶች ተመላክቷል፡፡ ከዚህ ከያዝነው እስትራቴጂክ ዕቅድ ከተመነዘሩት ውሰጥ የሶስት ዓመት የመካከለኛ ዘመን የሚተገበሩ ግቦች እና ተግባራትን የሚያመላክት ይህ መሪ ዕቅድ ተዘጋጅታል፡፡
•
•