የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ10 ዓመት (2013 - 2022) ስትራቴጂክ ዕቅድ

ጥቅምት 2013

Long-Term Fiscal Plans

የኢፌዴሪ መንግስት የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን በማውጣት በፖለቲካ፣
በማህበራዊና ኢኮኖሚ መስኮች የተያዙ ግቦችን ለማሳካት እንዲሁም የፍትህ ዘርፉን
የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የህብረተሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት በማስከበር የሕግ
የበላይነትን ለማረጋገጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ተቋሙ በሕግ የተሰጠው ተልእኮና
ኃላፊነት ተግባራዊ በማድረግ ሕዝብና መንግሥት የሚጠብቁትን ውጤት ለማሳካት
የመካከለኛ ዘመንና አጫጭር ዕቅዶች በማውጣት በርካታ ተግባራት አከናውኗል፡፡
በተለይም ሁለተኛው የአምስት ዓመት (2008-2012) ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በማውጣት የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ህገ መንግስቱንና የህግ መንግስታዊ ስርዓት በማክበርና በማስከበር፣ የህዝብንና የመንግስትን ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ በመሆኑም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እስካሁን ካከናወናቸው ተግባራት፣ ወሳኝ ስኬቶችና
ተግዳሮቶች በመነሳት መሰረታዊና ስትራተጂዊ እይታ የሚጠየቁ ጉዳዮች መኖራቸውና
በተቋሙ የተጀመረው የሕግና ፍትሕ የለውጥ ሂደት የተገኙትን ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ
ለማሸጋገርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የረጅም ጊዜ ስትራተጅያዊ ዕቅድ በማውጣትና
በመተግበር ስትራተጅያዊ አመራር መስጠት ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም የ10 ዓመት (ከ2013
እስከ 2022) ስትራተጂያዊ ዕቅድ መቅረጽና መተግበር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የሚዛናዊ
ውጤት ተኮር ስርአትን በመሳሪያነት በመጠቀም ይህ ስትራተጂያዊ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
ስትራቴጂያዊ ዕቅዱ በመንግስት የተነደፈውን የአስር አመት መሪ የልማት ዕቅድ
እንደመነሻ ይዞ የተነሳው ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት (African beacon of
prosperity) የማድረግ ራእይ ለማሳካትና ዜጎች ዘር፣ ሃይማኖ፣ እድሜና ፆታ ሳያግዳቸው
በማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያለምንም ተፅአኖ በእኩልነት እንዲሳተፉ ለማድረግ
የተመቻቸ የሕግ ማዕቀፍና አፈፃፀም እንዲኖር የሕግ የበላይነት ማረጋገጥ ዋነኛው የዕቅዱ
ምሶሶ በማድረግ በዚህ የረጅም ዘመን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ውስጥ ተቋሙን የሚመለከት
ሀገራዊ የዘርፉን ጉዳዮች ከተግባርና ሃላፊነቱ በመነሳት በስትራቴጂ ነድፎ መምራትና
ማስፈፀም አስፈላጊ በመሆኑ በግምገማ የተቀመጡትን መልካም አጋጣሚዎች አሟጦ
መጠቀም እንዲሁም ክፍተቶችና ፈተናዎችን በሚፈታ መልኩ ታሳቢ ተድርጓል፡፡

ስትራተጂያዊ ዕቅዱ አራት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን ጠቅላላ ሁኔታ በክፍል አንድ
የተቀመጠ ሲሆን፣ የተቋሙና አጠቃላይ የሁኔታ ግምገማና ትንተና በክፍል ሁለት፣ ጠቅላላ
ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣ የትኩረት መስኮችና ግቦች በክፍል ሦስት የተመላከቱ ሲሆን
የክትትልና ድጋፍ አግባቦች ደግሞ በክፍል አራት ተተንትነዋል፡፡ በመጨረሻም ዕቅዱን
ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ የሰው ኃይልና የበጀት ፍላጎት ትንበያ በአባሪነት ተያይዘዋል፡፡

ተጨማሪ ዕቅዶችና ሪፖርቶች

ጥቅምት፥ 2018 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports