የፍትህ ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም የዓመቱ የእቅድ አፈጻፀም ማጠቃለያ ሪፖርት

2015 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥና የወንጀል ህጉን ከማስከበርና የፌዴራል መንግስቱንና የህዝብን ፍትሐብሔራዊ መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ ፍትህ ከማስፈን አኳያ ሀገራዊ ተልዕኮውን ከማሳካት አንፃር ዘርፉ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፣ እያደረገም ይገኛል፡፡ በመሆኑም የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩን ውጤታማነት ከማሳደግና የህዝብና የመንግስት ጥቅም በማስጠበቅ ረገድም የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ውጤታማነት ለማሻሻል ጥረቶች ከመደረጋቸው ጋር ተያይዞ ህጎችን ከማርቀቅና ችግር ፈቺ ጥናቶችንና የንቃተ ህግ ትምህርትና ሥልጠናዎችን በመስጠት የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ ለማሳደግ፣ የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ዜጎች የነፃ የጥብቅና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ከመደረጉ በተጨማሪ የወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃንና የወንጀል ተጎጅዎችን አያያዝን ለማሻሻል ጥረት ተደርጓል፡፡ የህግ የበላይነትንና ሰብዓዊ መብትን በማክበርና በማስከበር፤ ወንጀልን በመከላከል፣ ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማስጠበቅ፤ የሕዝብ ዓመኔታ ያተረፈ ተደራሽ፣
ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት የሚስችሉ ተግባራትን እያከናወነ  ይገኛል፡፡ ይህንንም ተልእኮ ከግብ ለማድረስ ተቋማዊ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማሳካት የሚታዩ አንኳር ክፍተቶችን ለይቶ ለመቅረፍ እና በተቋሙ ደረጃ በተጀመረው የሕግና ፍትሕ ሪፎርም የተገኙትን ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የረጅም ጊዜ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በማውጣትና በመተግበር ስትራቴጅያዊ አመራር መስጠት የሚጠይቅ በመሆኑ የተቋሙ የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ እና የቀጣይ አምስት ዓመታት ዝርዝር ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ ከዚህ ስትራቴጂክ ዕቅድ ተመንዝረው በ2015 በጀት ዓመት የሚተገበሩ ግቦች እና ተግባራትን የሚያመላከት መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ለሁሉም የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ካስኬድ በማድረግ ከዚህ ዕቅድ የየራሳቸውን ዕቅድ በውጤት ተኮር ምዘና ሥርዓት በመንደፍ ለተግባራዊነቱ
ስትራቴጂና ዝርዝር ግቦችን ቀርጾው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት የተያዘውን ዕቅድ ተግባራዊ እያደረገና እንዲሁም የዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸሙን የክትትልና ድጋፍ አግባብን ለማጎልበት በየሩብ ዓመቱ በተለያየ ደረጃ በመገምገም ሊስተካከሉና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ተግባራት በመለየትና ዓመታዊ አውዱ በተሻለ ተነሳሽነትና የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ግቦች ላይ ትኩረት በመስጠት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡
የሪፖርቱ ይዘትም ክፍል አንድ- የአፅህሮተ ሪፖርት፣ ክፍል ሁለት፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ራዕይ ተልዕኮ፣ እሴቶችና የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም፤ ክፍል ሶስት፡- የእይታ መስኮች፣ ግቦችና ለግብ ማሳኪያ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ክፍል አራት፡- በእቅድ አፈጻጸም የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ፣ክፍል አምስት- የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ወይም መስኮች፣ ክፍል ስድስትበሩብ ዓመቱ የታዩ ችግሮችና የመፍትሄ ሀሳቦች ክፍል ሰባት – ቁልፍ አፈፃፀም አመላካቾች፣ መለኪያና ኢላማዎች ተካተው እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

ተጨማሪ ዕቅዶችና ሪፖርቶች

ጥቅምት፥ 2018 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports
መጋቢት 2015

Annual Fiscal Plans & Reports