የፍትህ ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት እቅድ

2015 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትህ ሚኒስቴር የተለያዩ እቅዶችን በማውጣት በፖለቲካ፤
በማህበራዊና ኢኮኖሚ መስኮች የተያዙ ግቦችን ለማሳካት እንዲሁም የፍትህ ዘርፉን
የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የብረተሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት በማስከበር
የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን
የማክበርና የማስከበር፣ የዜጎች ሰብአዊ ዴሞክራሲዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር፡
የወንጀል ህጎችንና የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ፖሊሲውን የማስፈጸም፣ የፌደራል
መንግስት ያወጣቸውን ህጎች ተፈፃሚነት ማረጋገጥ፤ የምስክሮችና ጠቋሚዎች
ጥበቃና ከለላ አዋጅ የማስፈፀም፤ የፌደራል መንግስት የሚያወጣቸውን ህጎች፣
የሚወስነውን ትላልቅ ውሳኔዎችና ብሄራዊ ጥቅምን የሚመለከቱ ግንኙነቶችን
የማማከር፤ የፌዴራል መንግስቱንና የሕዝብን ፍትሐብሄራዊ መብትና ጥቅም
ማስጠበቅ እንዲሁም በወ/ል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ተልዕኮ ተሰጥቶታል፡፡ ተቋሙ
ይህንን ተልእኮ ለመወጣት አደረጃጀትና አሰራር በመቅረጽ ሕዝብና መንግሥት
ከፍትሕ ዘርፉ የሚጠብቁትን ውጤት ለማሳካት ባለፈው እስትራቴጂክ የዕቅድ ዘመን
ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ሆኖም የፍትህ
ዘርፉ ሕዝብና መንግስት የሚጠብቁትን ውጤት ከማስመዝገብ አንፃር በርካታ
ጉድለቶች የሚስተዋሉበት መሆኑን ያለፉት የእቅድ ጊዜያት አፈፃፀም ግምገማ እና
በተለያዩ መድረኮች ከሕብረተሰብ ተወካዮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው
ውይይት ተመላክቷል፡፡
ስለዚህ በተቋሙ ሃላፊነቶች ዙሪያ የሚታዩ አንኳር ክፍተቶችን ለይቶ ለመቅረፍ እና
በተቋሙ ደረጃ በተጀመረው የሕግና ፍትሕ ሪፎርም የተገኙትን ውጤቶች ወደላቀ ደረጃ
ለማሸጋገርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የረጅም ጊዜ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በማውጣትና
በመተግበር እስትራቴጅያዊ አመራር መስጠት የሚጠይቅ በመሆኑ ተቋሙ የአስር
ዓመት መሪ ዕቅድ እና የቀጣይ አምስት ዓመታት ዝርዝር እስትራቴጂክ ዕቅድ
ተዘጋጅቷል፡፡ ከዚህ ከያዝነው እስትራቴጂክ ዕቅድ ተመንዝረው /ውስጥ/ በ2015 በጀት
ዓመት የሚተገበሩ ግቦች እና ተግባራትን የሚያመላክት ይህ መሪዕ ቅድ ተዘጋጅታል፡

መሪ እቅዱ በስድስት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን በክፍል አንድ የፍትህ ሚኒስቴር
ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች፣ በክፍል ሁለት የእቅዱ መነሻ ሁኔታ፣ ውስጣዊና ውጫዊ
የዳሰሳ ትንተና እና የአፈጻጸም ግምገማ፣ በክፍል ሦስት የዝግጅትና ትግበራ ምዕራፍ
ግቦችና ዋና ዋና ተግባራት ተመላክቷል፡፡ በክፍል አራት የተቋሙ ፕሮጀክቶችና
ለዕቅድ የማስፈጸሚያ የተመደበ በጀት፣ በክፍል አምስት የማስፈፀሚያ
እስትራቴጂዎች፣ ከትትልና ድጋፍ ስርአት እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና
የመፍትሔ ሀሳቦች የተመለከተ ሲሆን በመጨረሻም በክፍል ስድስት የድርጊት
መርሃ ግብር እንዲካተት ተደርጓል፡፡

ተጨማሪ ዕቅዶችና ሪፖርቶች

ጥቅምት፥ 2018 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports
መጋቢት 2015

Annual Fiscal Plans & Reports