•
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የህግ የበላይነትንና ሰብዓዊ መብትን በማክበርና በማስከበር፤ ወንጀልን በመከላከል፣ ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማስጠበቅ፤ የሕዝብ ዓመኔታ ያተረፈ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት የሚስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይህንንም ተልእኮ ከግብ ለማድረስ መንግስት የሚመራባቸውን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና አቅጣጫዎችን ለማሳካት የሚታዩ አንኳር ክፍተቶችን ለይቶ ለመቅረፍ እና በተቋሙ ደረጃ በተጀመረው የሕግና ፍትሕ ሪፎርም የተገኙትን ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የረጅም ጊዜ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በማውጣትና በመተግበር ስትራቴጅያዊ አመራር መስጠት የሚጠይቅ በመሆኑ የተቋሙ የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ እና የቀጣይ
አምስት ዓመታት ዝርዝር ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ ከዚህ ስትራቴጂክ ዕቅድ ተመንዝረው በ2014 በጀት ዓመት የሚተገበሩ ግቦች እና ተግባራትን የሚያመላከት መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ሁሉም የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ከዚህ ዕቅድ የየራሳቸውን
ዕቅድ በውጤት ተኮር ምዘና ሥርዓት በመንደፍ ለተግባራዊነቱ ስትራቴጂና ዝርዝር ግቦችን ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት የተያዘውን ዕቅድ ተግባራዊ እያደረገና እንዲሁም የዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸሙን የክትትልና ድጋፍ አግባብን ለማጎልበት በወርሃዊና በየሩብ ዓመቱ በተለያየ ደረጃ በመገምገም ሊስተካከሉና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ተግባራት በመለየትና አቅጣጫ በማሰቀመጥ፣ የአምስት ዓመቱን ዕቅድ በተሻለ ተነሳሽነትና የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ግቦች ላይ ትኩረት በመስጠት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በ2014 የበጀት የከናወኑ ተግባራቶች ሪፖርት የመረጃ
ምንጭ የመንግሥት ሕግና የፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ፤የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ እና የአስተዳደር ዘርፍ ያቀረቡትን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡ክፍል አንድ -የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ራዕይ ተልዕኮ፣ እሴቶች ፤ ክፍል ሁለት- የአፅህሮተ ሪፖርት ፤ ክፍል ሶስት- የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም፤ ክፍል አራት- በግቦች አተገባበር ምእራፍ የተከናዎኑ ዋናዋና ተግባራት ፤ክፍል አምስትበእቅድ አፈጻጸም የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ፤ክፍል ስድስት- ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ፣ ክፍል ሰባት- ማጠቃለያ ፣ ክፍል ስምንት- ስታስተሪካዊ ሠንጠረዦች እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
•
•