የፍትህ ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የዓመቱ የእቅድ አፈጻፀም ማጠቃለያ ሪፖርት

2013 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሀገራችን የሕዝብንና የመንግስትን ጥቅም በተሟላ ሁኔታ የሚያስጠብቅ፣ ሕጎች በሚገባ መደራጀታቸውንና የመንግስት ሥራዎች በሕግ መሠረት መመራታቸውን የሚያረጋግጥ የሕግ የበላይነትን የሚያስከብር የሕዝብ ተአማኒነት ያለው፣ በተሟላ ተቋማዊና ሙያዊ ነፃነት የሚያገለግል ለሙያዊ፣ ተቋማዊና ሕዝባዊ ተጠያቂነት የሚያግዝ ፣ በግልፀኝነትና አሳታፊነት የሚሰራ ወጥነት ያለው፣ ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ጠንካራ የሕግ አስከባሪ ዐቃቤ ሕግ ተቋም ለማደራጀት ታስቦ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 የተቋቋመ ተቋም ነዉ፡፡ ተቋሙ የህግ የበላይነትን
የማረጋገጥ ሀገራዊ ተልዕኮውን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን እየተካሄደ ያለውን ሃገራዊ ለውጥ ቀጣይነት ለማረጋገጥና የለውጥ ሂደቱን የሚመጥን የፍትህና የህግ ሪፎርም ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡ ሆኖም ሕዝብና መንግስት የሚጠብቁትን ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር በርካታ ጉድለቶች የሚስተዋሉበት መሆኑን ያለፉት ጊዜያት አፈፃፀም ግምገማ እና በተለያዩ መድረኮች ከሕብረተሰብ ተወካዮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት መረዳት ተችሏል፡፡
እነዚህን ክፍተቶች ለይቶ ለመቅረፍ እና በተጀመረው በሕግና ፍትሕ ሪፎርሙ የተገኙትን ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና የህዝብና የመንግስትን ጥቅም በላቀ ሁኔታ ለማስከበር እንዲሁም የህዝብ ሰላምና ደህንነት የሚጎዱ ልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ለመከላከልና ተፈጽመው ሲገኙ ወንጀለኞች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኘ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ያለፉት አስር አመታት (2003-2012) አፈፃፀም ሪፖርትና የ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም በመገምግም የቀጣይ የአስር ዓመት (2013-2022) መሪ ዕቅድ
፣የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ እና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አዘጋጅቶ በእቅዱ ፈፃሚ እና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ በዝግጅት ምዕራፉ የከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡

ተጨማሪ ዕቅዶችና ሪፖርቶች

ጥቅምት፥ 2018 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports
መጋቢት 2015

Annual Fiscal Plans & Reports