የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ5 ዓመት (2013-2017) ስትራቴጂክ ዕቅድ

ጥቅምት 2013

Long-Term Fiscal Plans

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሕግ የተሰጠው ተልእኮና ኃላፊነት ተግባራዊ በማድረግ
ሕዝብና መንግሥት ከፍትሕ ዘርፉ የሚጠብቁትን ውጤት ለማሳካት የመካከለኛ ዘመንና
አጫጭር ዕቅዶች በማውጣት በርካታ ተግባራት ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ባለፈው
ስትራቴጂክ የዕቅድ ዘመን የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ ህገ መንግስቱንና የህግ
መንግስታዊ ስርዓት በማክበርና በማስከበር፣ የህዝብንና የመንግስትን ጥቅም ዘርፈ ብዙ
ተግባራትን በማከናወን ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ሆኖም የፍትህ ዘርፉ ሕዝብና
መንግስት ከሚጠብቁት አፈፃፀም አንፃር በርካታ ጉድለቶች የሚስተዋሉበት መሆኑን
ያለፉት ጊዜያት አፈፃፀም ግምገማ እና በተለያዩ መድረኮች ከሕብረተሰብ ተወካዮችና
ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ተመላክቷል፡፡
ስለዚህ በዘርፉ የሚታዩ አንኳር ክፍተቶችን ለይቶ ለመቅረፍ እና በተቋሙ የተጀመረው
የሕግና ፍትሕ የለውጥ ሂደት የተገኙትን ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ቀጣይነቱን
ለማረጋገጥ የረጅም ጊዜ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በማውጣትና በመተግበር ስትራቴጅያዊ
አመራር መስጠት ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ አፈፃፀም የተለዩ ክፍተቶች ለመሙላት
በተቋሙ ከተዘጋጀው የ10 ዓመት ስትራተጂያዊ መሪ ዕቅድ በመነሳት የቀጣይ አምስት
ዓመታት (ከ2013 እስከ 2017) የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች፣
ዓላማዎች፣ ግቦች፣ ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች እና የማስፈፀሚያ ስልቶች እንዲሁም
የክትትልና ግምገማ ስርዓት የሚያመላክት ይህ ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅታል፡፡
ስትራተጂያዊ ዕቅዱ አራት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን በክፍል አንድ አጠቃላይ
ሁኔታን መሰረት በማድረግ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዳራ፣ የዕቅድ ዝግጀት ዘዴ እና የእቅድ
ዝግጅት ሂደት የተቀመጠ ሲሆን በክፍል ሁለት ሁኔታ ትንተና፣ በዘርፉ የተለዩ ዋና ዋና
አፈፃፀም ክፍተቶች፣ ክፍተቶችን ለመሙላት ዘርፉ የሚኖረው ሚና ተመላክቷል፡፡ በክፍል
ሶስት የስትራቴጂክ ዕቅዱ ዓላማ፣ የትኩረት መስኮች፣ ግቦችና ቁልፍ አፈፃፀም አመላካቾች
የተካተተ ሲሆን በክፍል አራት የክትትልና ድጋፍ ስርዓት፣ ስትራቴጅያዊ የአፈፃፀም
አቅጣጫዎች እና በዕቅድ ትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና መፍትሔዎች
ተመላክተዋል፡፡በመጨረሻው ዕቅዱን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ የሰው ኃይልና የበጀት
ፍላጎት ትንበያ በአባሪነት ተያይዟል፡፡

ተጨማሪ ዕቅዶችና ሪፖርቶች

ጥቅምት፥ 2018 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports
መጋቢት 2015

Annual Fiscal Plans & Reports